በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።1 እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብሩንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምንም እንዳትናወጥ አጸናት። 2 አቤቱ፥ ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ። 3 አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ። 4 ከብዙ ውኆች ድምፅ የተነሣ የባሕር እንቅስቃሴዋ ድንቅ ነው። ድንቅስ በልዕልና የሚኖር እግዚአብሔር ነው። 5 ምስክርህ እጅግ የታመነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤትህ ምስጋና ይገባል። |