La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 70 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 70

ርዳታን ለማግኘት የቀረበ ጸሎት (የመዝሙር 40፥13-17 ተመሳሳይ)

1 አምላክ ሆይ! አድነኝ! እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህም እርዳኝ!

2 ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ ግራም ይጋቡ፤ የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

3 እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

4 አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ ሐሴትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ዘወትር “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።

5 እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ አትዘግይ!

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia