La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 24

ታላቁ ንጉሥ

1 ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው።

2 ምድርን በባሕር ላይ የመሠረተው፥ ከውሃ በላይም ያጸናው እርሱ ነው።

3 ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤ በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል።

4 ይህን ማድረግ የሚችል፥ እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥ ጣዖትን የማያመልክ፥ ዋሽቶ የማይምል ነው።

5 እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል።

6 ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡና የያዕቆብን አምላክ ፊት የሚሹ እንደዚህ ያሉት ሰዎች ናቸው።

7 እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።

8 ይህ የክብር ንጉሥ ማነው? እርሱ ብርቱና ኀያሉ እግዚአብሔር ነው። እርሱ በጦርነት ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።

9 እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።

10 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ይህ የክብር ንጉሥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው!

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia