La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 127 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 127

ስለ እግዚአብሔር ቸርነት የቀረበ ምስጋና

1 እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ የቤት ሠሪዎች ድካም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የከተማ ጠባቂዎች ትጋት ከንቱ ነው።

2 በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።

3 ልጆች ከእግዚአብሔር የሚገኙ ስጦታዎች ናቸው፤ እውነተኛም በረከት ናቸው።

4 ሰው በወጣትነቱ የሚወልዳቸው ወንዶች ልጆች በወታደር እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው።

5 እንደነዚህ ፍላጻዎች የሆኑ ብዙ ልጆች ያሉት ሰው የታደለ ነው፤ ከጠላቶቹ ጋር በፍርድ አደባባይ በሚከራከርበት ጊዜ ከቶ አይሸነፍም።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia