መዝሙር 70 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መዝሙር 701 ለመዘምራን አለቃ፥ ለመታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር። 2 አቤቱ፥ አድነኝ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን። 3 ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጐስቁሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም። 4 እሰይ እሰይ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። 5 የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፥ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ። 6 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ አቤቱ፥ እርዳኝ፥ ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ፥ አትዘግይ። |