La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 67 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መዝሙር 67

1 ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።

2 እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፥

3 መንገድህንም በምድር፥ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን እናውቅ ዘንድ።

4 አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።

5 ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ።

6 አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።

7 ምድር ፍሬዋን ሰጠች፥ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።

8 እግዚአብሔር ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።

Mostrar Biblia Interlineal