La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መዝሙር 54

1 ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት።

2 ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ፥

3 አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ።

4 አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ የአፌንም ቃል አድምጥ፥

5 እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥ ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።

6 እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ጌታም ለሕይወቴ ደጋፊ ነው።

7 ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፥ በእውነትህም አጥፋቸው።

8 በፈቃዴ እሠዋልሃለሁ፥ አቤቱ፥ መልካም ነውና ስምህን አመሰግናለሁ፥

9 ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና፥ ዓይኔም የጠላቶቼን ውድቀት አይታለችና።

Mostrar Biblia Interlineal