La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መዝሙር 11


1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። በጌታ ታመንሁ፥ ነፍሴን፦ እንዴት እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ሽሺ ትሉአታላችሁ?

2 እነሆ ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።

3 መሠረቶቹ ከፈረሱ፥ ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?

4 ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

5 ጌታ ጻድቅንና ክፉን ይመረምራል፥ ዓመፃ የሚወደውን ግን ነፍሱ ትጠላለች።

6 በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።

7 ጌታ ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፥ ቅን ሰው ፊቱን ያየዋል።

Mostrar Biblia Interlineal