1 በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል። የጌታ ዛፍ ቅርንጫፍ2 በዚያን ቀን የጌታ ዛፍ ቅርንጫፍ ውብና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን 3 በጽዮን የቀሩት፤ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፤ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ፤ ኩራትና ክብርም ይሆናል። 4 ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል። 5 ከዚያም ጌታ በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፤ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤ 6 ከቀኑ ሙቀት ጥላና መከለያ፤ ከውሽንፍርና ከዝናብም መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናል። |