La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


ዘፀአት 11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ዘፀአት 11

ስለ መጨረሻው መቅሠፍት ማስጠንቀቂያ

1 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ ገና አንድ መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ በኋላ ከዚህ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።

2 ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።”

3 ጌታም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጠ። ሙሴም በግብጽ ምድር፥ በፈርዖን አገልጋዮች ፊትና በሕዝቡ ፊት እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ።

4 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በእኩለ ሌሊት እኔ በግብጽ መካከል እወጣለሁ፤

5 በግብጽም ምድር ያለ በኩር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባርያይቱ በኩር ድረስ፥ የከብቱም በኩር ሁሉ ይሞታል።

6 በግብጽ ምድር ሁሉ አስቀድሞ እንደ እርሱ ያልሆነ ኋላም ደግሞ የማይሆን ታላቅ ለቅሶ ይሆናል።

7 በእስራኤል ልጆች መካከል ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ውሻ ምላሱን አያንቀሳቅስባቸውም ይህም ጌታ በግብጽና በእስራኤል መካከል እንደለየ እንድታውቁ ነው።

8 እነዚህም አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፥ ለእኔም ይሰግዳሉ፥ ‘አንተ ውጣ በሥርህ ያለ ሕዝብ ሁሉ ይውጣ’ ይላሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።

9 ጌታም ሙሴን፦ “ተአምራቴ በግብጽ ምድር ብዙ እንዲሆን ፈርዖን አይሰማችሁም” አለው።

10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራቶች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ፤ ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፥ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ አልለቀቀም።

Mostrar Biblia Interlineal