እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ዐይንህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ” አለኝ። ዐይኔንም ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፤ እነሆም በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል በመግቢያው ይህ የቅንዓት ምስል ነበረ። ከዚያም ወደ ምሥራቅ ያስገባል።
ዘካርያስ 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህ የሚመጣው ምን እንደ ሆነ እይ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ “ዐይኖችህን አንሣ፥ ይህችም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ” አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም እንደገና ወደ እኔ መጥቶ “የሚመጣው ነገር ምን እንደ ሆነ ተመልከት!” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ። |
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ዐይንህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ” አለኝ። ዐይኔንም ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፤ እነሆም በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል በመግቢያው ይህ የቅንዓት ምስል ነበረ። ከዚያም ወደ ምሥራቅ ያስገባል።
ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ ስበክ እንዲህም በል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።
ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። እርሱም፦ እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው ብሎ መለሰልኝ።