ዳዊትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ ሲወጣም ያለቅስ ነበር፤ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፤ ያለጫማም ይሄድ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው ነበር፤ እያለቀሱም ይወጡ ነበር።
ዘካርያስ 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፣ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፣ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ታላቅ ሸለቆን በመሥራት የተራራውን እኩሌታ ወደ ሰሜን፣ እኩሌታውንም ወደ ደቡብ በማድረግ ምሥራቅና ምዕራብ ሆኖ ለሁለት ይከፈላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን የእግዚአብሔር እግሮች በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም በመካከሉ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ጥልቅ ሸለቆ ይሆናል፤ የተራራውም እኩሌታ ወደ ሰሜን፥ እኩሌታውም ወደ ደቡብ ይሸሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማል፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በሰፊ ሸለቆ በሁለት ይከፈላል፤ ስለዚህም የተራራው እኩሌታ ወደ ሰሜን እኩሌታውም ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፥ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፥ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል። |
ዳዊትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ ሲወጣም ያለቅስ ነበር፤ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፤ ያለጫማም ይሄድ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው ነበር፤ እያለቀሱም ይወጡ ነበር።
ከእግዚአብሔርም ፊት የተነሣ የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች፥ የምድረ በዳም አራዊት፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይገለባበጣሉ፤ ገዳላገደሎችም ይወድቃሉ፤ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
እነሆም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ መንገድ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተምም ነበር፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።
ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ እንደ ዓረባ ትሆናለች፣ እርስዋም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው በር ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።
በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል፣ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል።
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፣ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ።
እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል።