ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁ ሰዎች ጐስቋሎች ናቸው፤ አለኝታቸው ከንቱ ነው፤ ድካማቸውም፥ መከራቸውም ጥቅም የሌለው ነው፤ ሥራቸውም ከንቱ ነው፤
በእርግጥም ጥበብንና ሥነ ሥርዓትን ያቃለሉ ጐስቋሎች ናቸው፤ ተስፋቸው ከንቱ፥ ልፋታቸው መና፥ የጥረታቸው ውጤትም ትርፍ አልባ ነው።