መልአኩም እንዲህ አለው፥ “ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ መንገዱንም ዐውቃለሁ፤ በገባኤልም ዘንድ ነበርሁ።”
ሌላኛውም “አዎን አውቀዋለሁ፥ ብዙ ጊዜ ወደዚያ ተመላልሻለሁ፤ መንገዶቹን ሁሉ ደኀና አድርጌ አውቃቸዋለሁ፥ ብዙ ጊዜ ወደ ሜዶን ሄጃለሁ፥ የማርፈውም በሜዶን አገር በራጌስ በሚኖረው ወንድማችን በሆነው በገባኤል ቤት ነው፤ ከኤቅባጥና ወደ ራጌስ ሁለት ቀን ያስኬዳል፥ ምክንያቱም ራጌስ የምትገኘው በተራራው ላይ ሲሆን ኤቅባጥና ደግሞ በሜዳው መሃል ነው።”