ሕዝቡም ወደ ልዑል እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር፤ በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ሥርዐቱን እስኪጨርሱ ድረስ ይቅር በሚል በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ነበር፤ ሥርዐቱንም ያከናውኑ ነበር።
የጌታ ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ አምልኮው እስኪፈጸም ድረስ፥ በመሐሪው አምላክ ፊት ይጸለያሉ፥ ታላቁን አምላክ ይማፀናሉ፤