የኢዮስያስ መታሰቢያው በቀማሚ ብልሃት እንደ ተቀመመ ሽቱ ነው፤ እንደ ማርም በአፍ ሁሉ ጣፋጭ ነው፤ በመጠጥ ግብዣም ጊዜ እንደ ዘፈን ነው።
የኢዮስያስ ትውስት፥ በሽቶ ጠማቂው ጥበብ እንደተቀመጠ ዕጣን መዓዛው አይጠፋም፥ ለሁሉም አፎች እንደ ማር የሚጣፍጥ፥ በወይን ጠጅ ግብዣም ላይ እንደሚሰማ ጣዕመ ዜማ ነው።