በሙሴም ዘመን ከእነርሱ ጋር ይቅርታን አደረገ፤ እርሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ በጠላት ፊት ተከራከሩ፤ ሕዝቡንም በደልን ከለከሏቸው፥ ክፉ እንጕርጕሮንም አስተዉአቸው።
በሙሴ ዘመን ታማኝነቱን ያስመሰከረ፥ የኃያሉ እግዚአብሔር ተከታይ ነበር። እርሱና የዩፍኒ ልጅ ካሌብ ሕዝቡን በመቃወም፥ ኃጢአት እንዳይፈጽሙ በመጠበቅ፥ ዓመፃውንም በማብረድ ትክክለኛነታቸውን አሳይተዋል።