የመብረቁም ድምፅ ምድርን ያስፈራታል፤ የምዕራብም ነፋስ ሰውነትን ያደርቃታል፤ በረድንም እንደሚበርሩ ወፎች ይበትነዋል፤ አወራረዱም እንደ አንበጣ አወራረድ ነው።
የሰሜኑ ማዕበልና ዓውሎ ነፋስም እንዲሁ ናቸው።