አገልጋዮቹም ወደ እርሱ መጥተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነግርህ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ፦ ተጠመቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት።
ሩት 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፥ ከዚህም አትላወሺ፥ ነገር ግን ገረዶቼን ተጠጊ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ቦዔዝ ሩትን፣ “ልጄ ሆይ ስሚኝ፤ ከእንግዲህ ወደ ሌላ አዝመራ ሄደሽ አትቃርሚ፤ ከዚህም አትራቂ፤ ከሴቶች ሠራተኞቼ ጋራ እዚሁ ሁኚ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም ሩትን፦ “ልጄ ሆይ፥ ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፥ ከዚህም አትላወሺ፥ ነገር ግን አገልጋዮቼን ተከትለሽ ቃርሚ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ቦዔዝ ሩትን እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ! ስሚ እዚህ ያሉትን ሴቶች ሠራተኞችን ተከትለሽ ቃርሚ እንጂ ይህን እርሻ ትተሽ ለመቃረም ወደ ሌላ ቦታ አትሂጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም ሩትን “ልጄ ሆይ! ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፤ ከዚህም አትላወሺ፤ ነገር ግን ገረዶቼን ተጠጊ። |
አገልጋዮቹም ወደ እርሱ መጥተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነግርህ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ፦ ተጠመቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት።
“የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን አጨዳ አታጥሩ፤ ስታጭዱም የወደቀውን ቃርሚያ አትልቀሙ።
እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ እውነትን ሁሉ፥ ቅንነትንም ሁሉ፥ ጽድቅንም ሁሉ፥ ንጽሕናንም ሁሉ፥ ፍቅርንና ስምምነትንም ሁሉ፥ በጎነትም ቢሆን፥ ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ አስቡ።
እርስዋም፦ ከአጫጆቹ በኋላ በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ አለች፣ መጣችም፥ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ድረስ ቆይታለች፣ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም አለው።
ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፣ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፣ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ አላት።
እግዚአብሔርም ደግሞ፥ “ሳሙኤል! ሳሙኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሥቶ ዳግመኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። እርሱም፥ “አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ” አለው።