እግዚአብሔርም በደሉን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።”
ኀጢአቱን፣ ጌታ ከቶ የማይቈጥርበት ሰው ምስጉን ነው።”
ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው የተባረከ ነው።”
ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው የተባረከ ነው!”
ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።
ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖችም ክብር ይገባል።
እግዚአብሔርንም በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤