ሮሜ 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእናንተ ብዙ የደከመችላችሁን ማርያምንም ሰላም በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማሪያ ሰላምታ አቅርቡልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማርያም ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
በጌታችን ስም መከራ የተቀበሉትን የጢሮፊሞናንና የጢሮፊሞስን ወገኖች ሰላም በሉ። በጌታችን ስም ብዙ የደከመች እኅታችንን ጠርሴዳን ሰላም በሉ።
በቤታቸው ያሉትን ማኅበረ ክርስቲያንም ሰላም በሉ፤ ወዳጄ ኤጴኔጦስንም እንዴት ነህ? በሉ፤ ይኸውም በእስያ በክርስቶስ ላመኑ ሁሉ መጀመሪያቸው ነው።
ከዘመዶች ወገን የሚሆኑትን ከእኔ ጋር ያመኑ እንድራናቆስንና ዩልያንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክርስቶስን እንደ አገለገሉ ሐዋርያት ያውቁአቸዋል።
ወንድሞች ሆይ! በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ።
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።