ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ፥ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ፥ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸውን፥ ይህን ያደረግሁትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አልሰማህምን?
ሮሜ 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ፥ ነቢያትህን ገደሉ፤ መሠዊያዎችህንም አፈረሱ፤ እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ነፍሴንም ይሿታል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታ ሆይ፤ ነቢያትህን ገድለዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ሊገድሉኝም ይፈልጋሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ ሆይ! ነቢያትህን ገደሉ፥ መሠዊያዎችህን አፈራረሱ፤ እናም እኔ ብቻ ቀረሁ ነፍሴንም ይፈልጓታል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ኤልያስ “ጌታ ሆይ! ነቢያትህን ገደሉ፤ መሠዊያዎችህን አፈረሱ፤ እኔ ብቻ ቀረሁ፤ እኔንም ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ” ብሎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ሆይ፥ ነቢያትህን ገደሉ መሠዊያዎችህንም አፈረሱ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ነፍሴንም ይሹአታል። |
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ፥ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ፥ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸውን፥ ይህን ያደረግሁትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አልሰማህምን?
ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር።
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጼን አልተቀበላችሁም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል፤ በዚህም አልፈራችሁኝም።