አቤቱ የኀያላን አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው።
እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።
አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፦
እነርሱ “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ርስት የራሳችን እናደርጋለን” ብለው ነበር።
እነሆ፥ አሁን ለወሮታችን ክፋት ይመልሱልናል፤ ከሰጠኸንም ርስት ያወጡን ዘንድ መጥተዋል።
በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ ብፁዓን ናቸው፤ ለዓለምና ለዘለዓለም ያመስግኑሃል።
የምድያምን ሁለቱን አለቆች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬብንም በሱርኤራብ ገደሉት፥ ዜብንም በኢያፌቅ ገደሉት፤ የምድያምንም ሰዎች አሳደዱ፤ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ጌዴዎን አመጡ።
ዛብሄልና ስልማናም፥ “ኀይልህ እንደ ጐልማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን” አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፤ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ።