እግዚአብሔርን ዐሰብሁት፥ ደስ አለኝም፤ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች። የጠላቶቼን ሁሉ ሰዓቶች ዐወቅኋቸው
በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ። ሴላ
ድንኳኑ በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው።
በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥ ጋሻና ጦርን፥ ሌሎችንም የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ሰባበረ።
የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።
ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ይወስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረኩትም፤ ምርኮውም ብዙ ነበርና ምርኮውን እየሰበሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።
እግዚአብሔርም መልአኩን ላከ፤ እርሱም ጽኑዓን ኀያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
የአሕዛብ አለቆች ከአብርሃም አምላክ ጋር ተሰበሰቡ፤ የምድር ኀይለኞች ለእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብለዋልና።
ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።