ስለዚህ ዝንጉዎች በፍርድ፥ ኃጥኣንም በጻድቃን ምክር አይቆሙም።
ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ፊት፣ ኀጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር መቆም አይችሉም።
ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
ስለዚህ ክፉ ሰዎች በፍርድ ቀን ከፍርድ አይድኑም፤ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ አይገኙም።
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩምና። በከንቱ የሚበድሉ ሁሉ ዘወትር ይፈሩ።
ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ።
ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
እግዚአብሔር ፍርድን ማድረግ ያውቃል፤ ኀጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ።
ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።
በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኀጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፤ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤
አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፤
በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”
እንግዲህ ከዚህ ከሚመጣው ሁሉ በጸሎታችሁ ማምለጥ እንድትችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እንድትቆሙ ሁልጊዜ ትጉ።”