ምሳሌ 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤ የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ ያጣፈጥኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ና ያዘጋጀሁትን ምግብ ብላ! የጠመቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጣ! |
እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮች በሉ፥ ጠገቡም፤ የወንድሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከሩም፥ ልባቸው የጠፋ ነውና።
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”