La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልጄ ሆይ፥ ለራስህ ጠቢብ ብትሆን ለባልንጀራህም ጠቢብ ትሆናለህ፥ ክፉም ብትሆን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ይመስላል። እርሱም የሚበርር ዎፍን እንደሚከተል ነው። የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤ የሚሰማራባትን መንገድ ዘነጋ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች ምድርም ይሄዳል፤ የማያፈራና የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጠቢብ ብትሆን ጥበበኛነትህ ለራስህ ነው፤ ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ያው አንተው ነህ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጥበብ ቢኖርህ ጥቅሙ ለራስህ ነው፤ ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ራስህን ነው።

Ver Capítulo



ምሳሌ 9:12
13 Referencias Cruzadas  

በእ​ው​ነት እኔ ከበ​ደ​ልሁ፤ ስሕ​ተቴ ከእኔ ጋር ትኖ​ራ​ለች። የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ነገር ተና​ገ​ርሁ፤ ነገ​ሬም ስን​ፍና ነው እንጂ በየ​ጊ​ዜው አይ​ደ​ለም።


“አሁ​ንም መታ​ገሥ ትችል እንደ ሆነ፥ ፍሬ​ህም ይበጅ እንደ ሆነ እስኪ ጽኑ ሁን።


ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።


ሰው በድካሙ ለራሱ ይደክማል፥ ከራሱም ጥፋትን ያርቃል። ጠማማ ግን በአፉ ጥፋትን ይለብሳል።


ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል፥ ለሰነፎችም እንደዚሁ ቅጣት።


አሁ​ንም በም​ድር ሁሉ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያለ​ቀና የተ​ቈ​ረጠ ነገ​ርን ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሰም​ቻ​ለ​ሁና እስ​ራ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ጸ​ና​ባ​ችሁ እና​ንተ ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።


የቀሩት ወገኖች ሁሉ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።


ሁሉም ሸክ​ሙን ይሸ​ከ​ማ​ልና።


በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።