ምሳሌ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ሰዎች እናንተን እለምናለሁ፥ ቃሌንም ለሰዎች ልጆች እናገራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰዎች ሆይ፤ የምጠራው እኮ እናንተን ነው፤ ለሰው ልጆች ሁሉ ድምፄን ከፍ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተ ሰዎች፥ እናንተን እጠራለሁ፥ ድምፄም ወደ ሰዎች ልጆች ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰዎች ሆይ! እናንተን ሁሉ እጠራለሁ፤ ወደ ሰው ዘር ሁሉ እጣራለሁ፤ |
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲህ ወዶታልና።
እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም አዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ሆኜ ከተሾምሁለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቅዋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ፥
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ፍጹም የሚሆነውን ሰው እናቀርበው ዘንድ፥ እኛ የምናስተምርለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የምንጠራለትና የምንገሥጽለት፥ ሥራውንም በጥበብ ሁሉ የምንናገርለት ነው።