ምሳሌ 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የውኃ ምንጭህ ለአንተ ይሁንልህ፤ ከልጅነት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤ በልጅነት ሚስትህም ደስ ይበልህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፥ ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በወጣትነት ያገባሃት ሚስትህ እንደ ጥሩ የምንጭ ውሃ ስለ ሆነች ትባረክልህ፤ ከእርስዋም ጋር ደስ ይበልህ። |
በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሓይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።
“አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሂድ፤ ምንም ነገር አይጫኑበት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈቃዱ ይቀመጥ፤ የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት።