የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
ምሳሌ 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የነገርህን ጥበብ እንዳይንቅብህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሞኝ ጋራ አትነጋገር፤ የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞኝ ጆሮ ምንም አትናገር፥ በቃልህ ጥበብ ያፌዛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ የሞላበት ምክርህን ስለሚንቅብህ ለሞኝ ሰው ቁም ነገር አታጫውተው፤ |
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።
የኤፌቆሮስን ትምህርት ከተማሩ ፈላስፋዎች መካከልና ረዋቅያውያን ከሚባሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላስፎችም የተከራከሩት ነበሩ፤ እኩሌቶችም፥ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎችም፥ “ስለ ኢየሱስ ከሙታን ስለ መነሣቱም ሰብኮላቸዋልና የአዲስ አምላክ ትምህርትን ያስተምራል” አሉ።