ዐሳበ ክፉ ሰው ብዙ ያጠፋል፤ ጽኑ ደፋር ቢሆን ግን ነፍሱን ይጨምራል።
ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤ በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።
ንዴተኛ ሰው መቀጮ ይከፍላል፥ ብታድነውም ደግሞ ትጨምራለህ።
ግልፍተኛ ሰው ቢኖር የግልፍተኛነቱን ዋጋ እንዲያገኝ ተወው፤ አንድ ጊዜ ከችግሩ ልታወጣው ብትሞክር ሌላ ጊዜም እንዲሁ ማድረግህ አይቀርም።
ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋልና፥ ቅንዓትም ሰነፉን ያጠፋዋል።
ለተስፋ ይሆንህ ዘንድ ልጅህን ግረፍ፥ ለመሳደብ ግን እጅህን አታንሣ፥
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።