ምሳሌ 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢባን ከንፈሮች በዕውቀት የታሰሩ ናቸው፤ የሰነፎች ልብ ግን የጸና አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢባን ከንፈር ዕውቀትን ታስፋፋለች፤ የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፥ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት የሚስፋፋው በብልኆች እንጂ በሞኞች አይደለም። |
ሙሽሪት ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ የማር ወለላ ይንጠባጠባል፤ ከምላስሽም በታች ማርና ወተት አለ፥ የልብስሽም መዓዛ እንደ ዕጣን መዓዛ ነው።
አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል።