La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ የጽኑዓን መንገዶች ግን ጥርጊያ ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሰነፍ መንገድ በእሾኽ የታጠረች ናት፤ የቅኖች መንገድ ግን የተጠረገ አውራ ጐዳና ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት፥ የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሰነፍ መንገድ በችግር እሾኽ የታጠረ ነው፤ የቅን ሰው መንገድ ግን እንደ ተስተካከለ ጐዳና ነው።

Ver Capítulo



ምሳሌ 15:19
18 Referencias Cruzadas  

እግ​ሮቼ በቅ​ን​ነት ቆመ​ዋ​ልና፤ አቤቱ፥ በማ​ኅ​በር አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


አቤቱ፥ በጽ​ድ​ቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላ​ቶቼ መን​ገ​ዴን በፊ​ትህ አቅና።


የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኀጢአት ግን በክፉዎች ላይ ትወርዳለች።


ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።


ብልህ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ አላዋቂ ልጅ ግን እናቱን ያሰድባል።


ታካች ሰው በላኩት ጊዜ ያመካኛል፥ እንዲህም ይላል፦ “አንበሳ በመንገድ አለ፥ በአደባባይም ግድያ አለ።”


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።


በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።


አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን።


በሚያውቁ ፊት ሁሉ የቀና ነው፥ ዕውቀትንም ለሚያገኙ ሰዎች የቀና ነው።


ወደ ቀኝም ቢሆን ወደ ግራም ቢሆን በኋ​ላህ በዚህ መን​ገድ እን​ሂድ የሚ​ሉና የሚ​ሳ​ሳቱ ሰዎ​ችን ድምፅ ጆሮ​ዎ​ችህ ይሰ​ማሉ።


በዚ​ያም ንጹሕ መን​ገድ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ደሰ መን​ገድ ይባ​ላል፤ በዚ​ያም ንጹ​ሓን ያል​ሆኑ አያ​ል​ፉ​በ​ትም፤ ርኩስ መን​ገ​ድም በዚያ አይ​ኖ​ርም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትም በእ​ርሱ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ሳ​ሳ​ቱ​ምም።


እር​ሱም፥ “በፊቱ፥ መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መን​ገድ ዕን​ቅ​ፋ​ትን አስ​ወ​ግዱ” ይላል።