ምሳሌ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ ቂሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ሞኞች ግን ጥበብና ሥነ ሥርዓትን ይንቃሉ። |
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።
ጠብቁት፤ አድርጉትም፤ ይህን ሥርዐት ሁሉ ሰምተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤