ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፤ ለሁላችንም አንድ ከረጢትና አንድ አቁማዳ ይሁንልን” ቢሉ፥
ከእኛ ጋራ ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣
ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፥ ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ”፥
ና ከእኛ ጋር ተባበር፤ በስርቆትና በቅሚያ የምናገኘውን ሀብት በኅብረት እንጠቀምበታለን።”
ብዙ ሀብቱን እንሰብስብ፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሙላ፤
ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፤
ከተሳዳቢዎች ጋር ምርኮን ከሚካፈል፥ በትሕትና ቍጣን የሚያርቅ ይሻላል።