ዘኍል 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን አበራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹ በመቅረዙ ላይ ሆነው ፊት ለፊት እንዲያበሩ አስቀመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮንም እንዲህ አደረገ፤ በመቅረዙ ፊት ለፊት እንዲበሩ በማድረግም መብራቶቹን አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። |
የመቅረዝዋም ሥራዋ እንዲህ ነበረ። ሁለንተናቸው ወርቅ የሆነ አፅቆችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበቦችዋም ሁለንተናቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዝዋን እንዲሁ አደረገ።