ዘኍል 7:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባተኛውም ቀን የኤፍሬም ልጆች አለቃ የኤሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ መባውን አቀረበ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛው ቀን የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ቀን የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አቀረበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከኤፍሬም ነገድ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማዕ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ቀን የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ |
“በባሕር በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የኤሜሁድ ልጅ ኤሌሳማ ነበረ።
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መባ ይህ ነበረ።
መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑ ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤