ዘኍል 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ መባውን አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛው ቀን የዛብሎን ሕዝብ አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ አቀረበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከዛብሎን ነገድ የሔሎን ልጅ ኤሊአብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፤ |
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሰገር ልጅ የናትናኤል መባ ይህ ነበረ።
መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤