ወደ እርሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም በለዓምን አለው፥ “እግዚአብሔር ምን አለ?”
ዘኍል 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምሳሌም ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ ስማ፤ የሶፎር ልጅ ሆይ፥ ምስክር ሁነህ አድምጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “ባላቅ ሆይ ተነሣ፤ ስማኝ፤ የሴፎር ልጅ ሆይ አድምጠኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ! ተነሣ፥ ስማም፤ የሴፎር ልጅ ሆይ! አድምጠኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤ “የጺጶር ልጅ ባላቅ ሆይ፥ ወደዚህ ቀረብ ብለህ የምነግርህን ሁሉ ስማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ ስማ፤ የሴፎር ልጅ ሆይ፥ አድምጠኝ፤ |
ወደ እርሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም በለዓምን አለው፥ “እግዚአብሔር ምን አለ?”
እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን?
ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም።