እርሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግዚእብሔርም የሚነግረኝን እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ የሞዓብ አለቆችም በበለዓም ዘንድ አደሩ።
ዘኍል 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም ባላቅን አለው፥ “በዚህ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ እሄዳለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም ባላቅን፣ “እርሱን ለመገናኘት ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እኔ ወደዚያ ጌታን ለማግኘት ስሄድ በዚህ በሚቃጠለው መሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም ባላቅን “አንተ እዚህ በሚቃጠለው መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ወደዚያ እሄዳለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅንም፦ እኔ ወደዚያ ለመገናኘት ስሄድ በዚህ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ አለው። |
እርሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግዚእብሔርም የሚነግረኝን እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ የሞዓብ አለቆችም በበለዓም ዘንድ አደሩ።
በሜዳ ወደ ተገነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰደው፤ አዞረውም፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን፥ አንድም አውራ በግ አሳረገ።
በለዓምም ባላቅን፥ “በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግዚአብሔር ቢገለጥልኝ፥ ቢገናኘኝም እሄዳለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ቃል እነግርሃለሁ” አለው። ባላቅም በመሠዊያው ዘንድ ቆመ፤ በለዓም ግን እግዚአብሔርን ይጠይቅ ዘንድ አቅንቶ ሄደ።