በመጀመሪያም የይሁዳ ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን አለቃ ነበረ።
ዘኍል 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺሕ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደየክፍላቸው በይሁዳ ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበር። በመጀመሪያ የሚጓዘው ይህ ቡድን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ። |
በመጀመሪያም የይሁዳ ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን አለቃ ነበረ።