የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በየዓላማዎቻቸው ሰፈሩ፤ እንዲሁም በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።
ዘኍል 2:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሌዋውያኑ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ አልተቈጠሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያን ግን ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ከሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ ጋር አልተቈጠሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። |
የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በየዓላማዎቻቸው ሰፈሩ፤ እንዲሁም በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።