ዘኍል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም አጠገብ የብንያም ነገድ ይሆናል፤ የብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፣ የብንያም ሕዝብ አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ቀጥሎ የብንያም ነገድ ነበረ፤ የብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፤ የብንያም ነገድ መሪ የጊድዖን ልጅ አቢዳን ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነርሱም አጠገብ የብንያም ነገድ ይሆናል፤ የብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ። |
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የጋዴዮን ልጅ የአቢዳን መባ ይህ ነበረ።