በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና።
ዘኍል 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጉባኤውም በሚሰበሰብበት ጊዜ ያለ ምልክት ትነፉታላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኅበሩን ለመሰብሰብ መለከቶች ይነፉ፤ ነገር ግን ድምፁ አይጩኽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉባኤውም በሚሰበሰብበት ጊዜ ንፉ፥ ነገር ግን የማስጠንቀቂያውን መለከት ከፍ ባለ ድምፅ አታሰሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኅበሩን በአንድነት እንዲሰበሰቡ ለማድረግ መለከት ትነፋለህ፤ ነገር ግን የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አታሰማም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጉባኤውም በሚሰበሰብበት ጊዜ ንፉ፥ ነገር ግን ድምፁን ከፍ አታድርጉት። |
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና።