አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
ማቴዎስ 8:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! አድነን፤ ጠፋን፤” እያሉ አስነሡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ቀሰቀሱትና፣ “ጌታ ሆይ፤ ጠፋን፤ አድነን!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፥ አድነን፤” እያሉ ቀሰቀሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፤ አድነን!” ብለው ቀሰቀሱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት። |
አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ” አለው።
ቀርበውም፥ “መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ልንጠፋ ነው” ብለው ቀሰቀሱት፤ ተነሥቶም ነፋሱንና የውኃዉን ማዕበል ገሠጻቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።