ማቴዎስ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ለመቶ አለቃ “ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም መቶ አለቃውን፣ “ሂድ! እንደ እምነትህ ይሁንልህ” አለው። ብላቴናውም በዚያች ቅጽበት ተፈወሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ለመቶ አለቃው “ሂድና እንደ እምነትህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ፥ ኢየሱስ የመቶ አለቃውን “ሂድ፤ እንደ እምነትህ ይሁንልህ” አለው። አገልጋዩም በዚያኑ ሰዓት ተፈወሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ለመቶ አለቃ፦ ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። |
ኢየሱስም “ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ወደዚያ እለፍ፤’ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።
ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።