La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወይም ወንድምህን ‘ከዐይንህ ጕድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ’ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዐይንህ ምሰሶ አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወይም በዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን፣ ‘ዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ ማለት እንዴት ትችላለህ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይም እነሆ በዓይንህ ምሰሶ እያለ ወንድምህን ‘ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣልህ ፍቀድልኝ’ እንዴት ትለዋለህ?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ደግሞስ በአንተ ዐይን ግንድ እያለ፥ ወንድምህን ‘እስቲ በዐይንህ ያለውን ጒድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 7:4
5 Referencias Cruzadas  

እናንተ ዕውሮች መሪዎች! ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።


በወንድምህም ዐይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፤ በዐይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?


አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ ከዐይንህ ምሰሶውን አውጣ፤ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዐይን ጕድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።


ወን​ድ​ም​ህ​ንም፦ ወን​ድሜ ሆይ፥ ታገሥ፤ በዐ​ይ​ንህ ያለ​ውን ጕድፍ ላው​ጣ​ልህ ልት​ለው እን​ደ​ምን ትች​ላ​ለህ? አንተ ግን በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይም፤ አንተ ግብዝ፥ አስ​ቀ​ድሞ ከዐ​ይ​ንህ ምሰ​ሶ​ውን አውጣ፤ ከዚህ በኋላ በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ታወጣ ዘንድ አጥ​ር​ተህ ታያ​ለህ።