ማቴዎስ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾኽ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ በለስ ይለቀማልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም የምታውቁአቸው በሥራቸው ፍሬ ነው። ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ የበለስ ፍሬ ይለቀማልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? |
ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ፤” ይላል።
እግዚእብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፤ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።