La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ዙሪያ ካለው አገር ሁሉ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይጐርፉ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም፥ ከይሁዳ ሁሉና በዮርዳኖስም ዙሪያ ካሉ አውራጃዎች ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም ከመላው የይሁዳ ምድር፥ ከዮርዳኖስም ዙሪያ ሁሉ፥ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤

Ver Capítulo



ማቴዎስ 3:5
9 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ከገሊላም ከዐሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።


የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።


“ኦሪ​ትም ነቢ​ያ​ትም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ዮሐ​ንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ይሰ​በ​ካል፤ ሁሉም ወደ እር​ስዋ ይጋ​ፋል።


ስለ ኀጢ​አት ስር​የት ለን​ስሓ የሚ​ያ​በቃ ጥም​ቀ​ትን እየ​ሰ​በከ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አው​ራጃ ዞረ።


ዮሐ​ን​ስም ሊያ​ጠ​ም​ቃ​ቸው የመ​ጡ​ትን ሰዎች እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ፉ​ኝት ልጆች፥ ከሚ​መ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ታመ​ልጡ ዘንድ ማን ነገ​ራ​ችሁ?


ዮሐ​ን​ስም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሳ​ሌም አቅ​ራ​ቢያ በሄ​ኖን ያጠ​ምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበ​ርና፤ ብዙ ሰዎ​ችም ወደ እርሱ እየ​መጡ ያጠ​ም​ቃ​ቸው ነበር።


እርሱ የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​በራ መብ​ራት ነበረ፤ እና​ን​ተም አን​ዲት ሰዓት በብ​ር​ሃኑ ደስ ሊላ​ችሁ ወደ​ዳ​ችሁ።