ማቴዎስ 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን፤’ አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዘግየት ብለው ሌሎቹ ልጃገረዶች መጥተው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ የቀሩቱ ደናግል መጥተው ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በኋላም የቀሩት ልጃገረዶች መጡና፦ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቍኦነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ። |
ባለቤቱ ተነሥቶ ደጁን ይዘጋልና፤ ያንጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈትልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀምራሉ፤ መልሶም፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላቸዋል።